በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:15)
1BIBLE
በመጀመሪያ እግዚአብሔር.........................................

ሕዳር 12 የሚካኤል ወይስ የአስፈሪው የዙሐል ጣኦት ቀን??

                          
                    የሁላችን እናት ቤተ-ክርስቲያን ኦርቶዶክስ ለሐገራችን በተለያዩ ጉዳዮች መልካም የሚባሉ ትውልድም ከቶ ሊክዳቸው የማይችል ታካዊና መንፈሳዊ በረከቶችን ጥላ የኖርች ጥንታዊትና ታላቅ ቤተ-ክርስቲያን ናት፡፡ የፊደል ገበታዎችን ቀርጻ ለሀገራችን ያበረከተች፤ የኪነጥበብ የአጻጻፍ ስልትን የቀመረች፣ የራሳችንን የመነጋገርያ ቋንቋ የሰጠችን፣ የዜማና የቅኔ ስልቶችን የፈጠረች፣ ከማንም ሳትኮርጅ የራሷን ድንግልና ጠብቃ የባሕል የወግል ልምዶችን ይዛ ዘመን የተሻገረች እንዲሁም ልዩ ልዩ ታረካዊ ቅርጾች ሰርታ ያቆየችን እሰከዚህ ትውልድ ድረስ በብዙ ፈተናና እንግልት በብዙ ድካም ጠብቃ ያበረከተችን ታላቅ ቤተ-ክርስቲያን መሆኑዋን ማንም ሊክደው አይችልም!!
ይሁንም እንጅ ይህን ያክል መልካም ሰራ እንደሰራች ሁሉ በዛው ልክ ደግሞ እንደውም ባለፈ ሁኔታ፣ ብዙ ትውልድን የሚያጠፋ፣ ከእግዚአብሔርም ክብር የሚጎድል ኑፋቄ፣ በአንዳንድ ከሰይጣን ጋር ህበረት ባለቸው፣ ጥንቆላንና ድግምትን መተዳደሪያ ብለው በያዙ ሰዎች ተበርዛና ተከልሳ የቀደመ መልኳንና ወዟን አጣ ትገኛለች፡፡ ይህም ብቻ አልበቃ ብሎ በአሁኑ ባለው ምስኪን ትውልድ ላይ የእነዚህ ትውልድ ገዳይ ኑፋቄዎችን በአደባባይ ሲነገርና እንደ ህጻን ልጅ በማባበል ምስኪኑ ሕዝብ ሲጋት እናያለን፡፡ ተሃድሶ ተሃድሶ… ያስፈልጋታልለቤተ-ክርስቲያናችን እያሉ የሚጪኹትን ዕንቁ ልጆቿን በእነዚህ ኑፋቄ ትምህርት የተጠመቁ አንዳንድ የዘርዓ ያዕቆብ ርዝራዥ ሰዎች “መናፍቅ” በሚል ስም ሲያባሩአቸውም እናስተውላለን፡፡ ቁም ነገሩ ግን ቢመችም ባይመችም ተሃድሶ ለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የግዷን ያስፈልጋታል!!! ቤተ ክርስቲያኗን በጥልቅ ከበረዟት ትምህርቶች መካከል በንጉስ ዘርዓ ያዕቆብ እና በተከታዮቹ ደብተራዎች የተጻፉት ድርሳናት፣ ታምራት፣ ታሪኮች… ወዘተ ይገኙበታል፡፡ ኑፋቄ ጠለቀባቸው ዘግናኝ መጽሐፍት መካከል አንዱ ‹‹መጽሐፈ ዚቅ›› ነው፡፡ ተመልከቱ እንግዲህ፤- “ሚካኤል አምላክ ወይስ መላክ?” ተብሎ አንድ ክርስቲያን የጌታን ቃል ያመነ እግዚአብሔርን አምለኩ አድረጎ በልቡ የሾመ ሰው ቢጠየቅ **የህጻናት ቀልድ እንጅ የምር ጥያቄ** አይመስለውም፡፡ የሚገርመው የመስከረም የሚካኤል ዚቅ እንዲህ ይላል፡-
o “መፈትው እንከ አኀውየ ንግበር በአለነ በኩለሄ በታህተ ሰማይ ንፌኑ ስብሃተ ፍሬ ከናፍሪነ እስመ ሚካኤል እግዚእነ” ትርጉሙም “ወንድሞቼ ከሰማይ በታች በሁሉ ስፍራ በአላችንን እናከብር ዘንድ ይገባናል፡፡ የከንፈራችንን ፍሬ ምስጋናን እንላክ፡፡ ሚከኤል ጌታችን ነውና” ይላል፡፡ በዚህ ቃል ውስጥ የምናገኛቸው ፈር የለቀቁ ከእውነትም የራቁ ድፍረትን የተቀላቀሉ በቀላሉ 3 ኑፉቄዎችን እናገኛለን፡-
1. ከሰማይ በታች ያለ ሰው ሁሉ የሚካኤልን በአል ያክብር ማለቱ!! እስቲ እንግዲህ የሚካኤል በዓል እየተባለ በሃገራችን የሚከበረው መቼ ተጀመረ፣ እንዴት ተጀመረ፣ ለምን ተጀመረ ብለን ስንጠይቅ፡- ከቤተ ክርስቲያኗ መጽሐፈት የሆነው “መጽሐፈ ጽድቅ በአለ ሐይማኖት በገጽ 152-153” እንዲህ ይነበባል፡፡ በግብጽ ሐገር ብዙ ቁጥር ያላቸው ጣዖታት ይመለኩ ነበር፡፡ ከነዚህም መካከል አንዱ “ዙሐል” የሚባል ስም ነበረው እጅግ አሰፈሪ ጣኦት ነበረ፡፡ በሃገሩ የነበሩ የዘመኑ ጳጳስ ‹‹ቅዱስ ማርቆስ›› ብዙዎችን ጣዖታት ከጠፉ በሆላ **ዙሐል የተባለው ጣኦት** ግን ሕዝቡ ያከብረውና ይፈራው ስለነበረ ለማጥፋት አልቻሉም፡፡ ከሳቸውም በሆላ የተሸሙ ጳጳሳትም በሙሉ እንደርሳቸው ሕዝቡን በመፍራት ሳያጠፉት ቆይተው በ300 ዓ/ም የተሾሙት ‹‹አባ እለ እስክንድሮስ›› የተባሉት ጳጳስ ግን ሕዝቡን ከጣዖታት ከመመለስ ይልቅ መንፈሳዊ ሽፋን የለበሰ ነገር ግን የበለጠ ኑፋቄ የሚያስፋፋ ግፍ ፈጸሙ፡፡ **ዙሐል የተባለውን አስፈሪ ጣኦት** ከሙኩራብ ጣኦትነቱ ተነስቶ በምትኩ የቅዱስ ሚካኤል ታቦት እንዲገባ አድርገው፤ የዙሐል ጣዖት በየዓመቱ ሕዳር 12 ቀን ይከበር ስለነበር ሕዝቡን ለማስደሰት ሲሉ ብቻ በዛው በሕዳር 12 ቀን የሚካኤል ታቦት ይከበር በማለት አወጅ አስነግረው አጸደቁ ይለናል፡፡ በአስፈሪው የዙሐል ጣኦት ምትክ የሚካኤል ታቦት የተባለውን በማስገባት ሕዝቡን አታለው መንፈሳዊ ሽፋን ሰጠው ሌላ በዓድ አምልኮን አስጀመሩ!! ማየት ማመን ነውና ሂደው መጽሐፉን ያንብቡት፡፡ ለዚህ ዘግናኝ ታሪክ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንተና አያስፈልገውም!! ኑፋቄ በአንድ ቃል ይዘጋልና እሱም ‹‹ኑፋቄ›› ተብሎ!!! የጌታ ቃል እንዲህ ይላል፡- ሮሜ 14፡-6 “ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል” ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ ደግሞስ በቅዱሳን ስምና በሰናያ ባሉ ቅዱሳን መላዕክት ስም ታቦት ማስቀረጹ፣ ከዚያም ሲያልፍ በስማቸው መባቻን ማድረጉ፣ ቀን መቆጠሩ፣ ዕጣን ማጨሱ ምን የሚሉት ነው?? ጌታ አምላካችን እግዚአብሔር እንዲህ ዓይነቱን ኑፋቄ ከሕዝባችን ልብ ጠራርጎ ያውጣልን!! ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ተሃድሶ ሐይማኖት ሳይሆን እግዚአብሔር ያስጀመረው ተልዕኮ ነውና ለቤተ-ክርስቲያናችሁ ዛሬውኑ ተነሱ!! ይህ መልካም የዘመኑ ጥሪ ነው!! ዓላማውም ቤተ ክርስቲያኗን ማጥፋት ሳይሆን ወደ ቀደመ መልኳና ውበቷ መመለስ ነው እንጅ!!! ዓላማው መቃብር ስር መኖሪያቸውን ያደረጉ፣ ቤተ ክርስቲያኗን በኑፋቄ የበረዙ፣ የዲያብሎስ አገልጋዮችን በእግዚአብሔር ቃል መገሰጽና ወደ ቃሉ መልካም ጌታ መማረክ ነው፡፡ ደግሞም የምዕመኑን ልብ በፍጡራን የሚታመነውን፤ እግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ ይዱኑ ዘንድ ከሰማይ በታች ወደ ሰጠው ወደ ታረደው በግ ወደ ናዝሬቱ ጌታ ኢየሱስ መመለስ ነው፡፡ ተሃድሶም እየሆነ ነው ደግሞም ይሆናል!!
2. የከንፈራችንን ፍሬ ምስጋናን ለሚካኤል እንላክ ማለቱ!! በእውኑ የከንፈር ፍሬ ወይም ምስጋና ለማን ይገባል? ለመላክ ወይስ ለሕያው አምላክ ለጌታ እግዚአብሔር??? የጌታ ቃል በዕብራውያን 13፡-15 እንዲህ ይላል “እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መስዋት ማለትም ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ በእርሱ እናቅርብለት” ይላል፡፡ በእውነቱ ሚካኤልም ይህን የከንፈር ፈሬ መስዋት ተቀበል ሲባል ቢሰማ እንዲህ አይነቱን ምንፍቅና ከቶ ሊቀበለው አይችልም!!! ምክንያቱም የቀድሞው መላክ ዲያብሎስ የወደቀበትን ምስጥር መቼ ይዘነጋና???
3. ሚካኤል ጌታችን ነውና ማለቱ!! ይህ መቼም ክርስቲያን ነኝ ከምትል ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታዬና አምላኬ ብላ ካመነች ቤተ እምነት የሚጠበቅ አይደለም!!! ሲቀጥል ደግሞ ድፍረት የተቀላቀለበትና ትውልድን የሚያስረግም፣ እግዚአብሔርም እንዲሁ ከገለጠው ክብር የሚያጎድል ተራ ምንፍቅና ነው፡፡ የጌታ ቃል እንዲህ ይላል ስለመላዕክት ዕብ 1፡-6 “የእግዚአብሔር መላዕክት ሁሉ ለእርሱ ይስገዱ… መላእክቱን መናፍስት አገልጋዮችን የእሳት ነበልባል የሚያደርግ” ይልና፤ ስለ ልጂ ኢየሱስ ግን ቁጥር 8-10 ላይ “አምላክ ሆይ ዙፋንህ እስከዘላለም ድረስ ይኖራል፡፡ የመንግስትህ በትር የቅንነት በትር ነው… ጌታ ሆይ አንተ ከጥንት ምድርን መሰረትክህ ሰማዮችም የእጆችህ ስራ ናቸው፡፡ እነርሱም ይጠፋሉ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፡፡ ሁሉም እንደልብስ ያረጃሉ እንደመጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ፡፡ ይለወጡማል አንተ ግን አንተ ነህ፡፡ ዓመታቶችህም ከቶ አያልቁም” ሲል ያስቀምጥልናል፡፡ አሜን አሜን!!!
እንግዲህ ምን እንላለን? መላዕክቱ ሁሉ ታዘዋልና ለጌታቸው ለእግዚአብሔር የክብርን ዜማ ያቀርባሉ እንጅ እነርሱ ጌቶች ሆነው፤ ምስጋናን አምልኮን ከሰው ልጆች አይቀበሉም!! ይህን ማስተማር በራሱ የእግዚአብሔርን ቃል መጣስና መቃረን ደግሞም መናፍቅ መሆን ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን መገዳደር ነው!!!

 
ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት። እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:5)
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free