በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:15)
1BIBLE
በመጀመሪያ እግዚአብሔር.........................................

JESUS ኢየሱስ

ኢየሱስ በቁርአን

መግቢያ 

ይህ ገጽ በቁርኣን ሙስሊሞች ስለ ዒሳ (ኢየሱስ) ካላቸው እይታ በመነሳት የተጻፉ መረጃዎች ናቸው። የራስህን ቁርአን በመመልከት፡ የሚከተሉትንም ግንዛቤዎች ትክክለኛነት አመሳክር።

በቁርአን ውስጥ ኢየሱስ አምላክ፡ የእግዚአብሔር ልጅ ወይም በመስቀል የሞተ ሰው አይደለም። በቁርአን ውስጥ ኢየሱስ አይሁዶች ያልተቀበሉትን መልዕክት ያመጣ ነቢይ ነው። እርሱ መሲሕ ተብሏል፡ ነገር ግን ያ ማለት የእግዚአብሔር መልእክተኛ ለማለት ብቻ ነው (ቁርኣን 4:171)። ወንጌልን አመጣ (ቁርኣን 57:27)።
ተአምራዊው የኢየሱስ መፀነስ 

በኢየሱስ ሕይወት በጣም የሚያስደንቀው የእርሱ መፀነስና መወለድ ነው፡ በቁርኣን 19፡16-26 ይገኛል። ስለዚህም ኢየሱስ በተአምራዊ መንገድ ነው የተወለደው፡ ምክንያቱም ይህ የተፈጸመው ወንድ የሚባል ጣልቃ ሳይገባበት ነውና። ይህም የኢየሱስ ተአምራዊ አወላለድ ወደ አንድ ጥያቄ ይመራል፡ ኢየሱስ ሰው ብቻ ነው ወይስ መንፈስ ብቻ ነው? ኢየሱስ ልክ እንደ አዳም ስለ ተፈጠረ ሰው ብቻ አልነበረምን? አዎን፡ በእርግጥ፡ በቁርኣን 3:59 የአዳም ልደትና የኢየሱስ ልደት ሲመሳሰል እናነባለን። ‘በእርግጥ የኢየሱስ ጉዳይ በአላህ ፊት ልክ እንደ አዳም ነው። እርሱ (አላህ) ከአፈር ፈጠረው እንዲህም አለው ‘ሁን’ ሆነም’።

ይሁን እንጂ ቁርአን ስለሚመሳሰልበት ገጽታ ብቻ አይነግረንም፤ በአዳም አወላለድና በኢየሱስ አወላለድ ደግሞ ስላለውም ልዩነት ይነግረናል እንጂ።

አዳም ያለ ሰብአዊ አባት ወይም እናት ነው የተወለደው (ቁርኣን 2:30፤ 15:28፤ 32:7)።
ኢየሱስ የተወለደው ከድንግል ነው (ቁርኣን 19፡20-22)።
አዳም የተፈጠረው ከታች ነው፡ ከአፈር ብቻ፡ ስለዚህም ምድራዊ ነው (ቁርኣን 15:28፤32:7)።
ኢየሱስ የተፈጠረው ከአንድ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡ ስለዚህም ሰማያዊ ነው (ቁርኣን 3:45)።
ኢየሱስ ለማርያም ሲሰጣት ጉድለት እንደሌለው ከእግዚአብሔር እንደ ተሰጠ ልጅ ሆኖ ነው (ቁርኣን 19:19)።

በነዚህ ተጨባጭ ነገሮች መሠረት በአዳምና በኢየሱስ ልደት መካከል የጎሉ ልዩነቶች አሉ ለማለት እንችላለን። አዳም የተፈጠረው ከታች ነው ኢየሱስ ደግሞ የተፈጠረው ከላይ ነው። ኢየሱስ ጉድለት የሌለውና በአንድ በእግዚአብሔር ቃል የተፈጠረ ስለ ሆነ ከፍ ያለ ማንነት አለው። በእግዚአብሔር ቃልና (ካሊማ) በመጻሕፍት ባሉት በእግዚአብሔር ቃላት መካከል እንለያለን። የእግዚአብሔር ቃልና መንፈስ ዘልዓለማዊ ናቸው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ያለ ቃልና ያለ መንፈስ ኖሮ አያውቅም። እንደ ቁርአን አባባል ኢየሱስ በምድር ኑሮው ጉድለት አልነበረውም (ቁርኣን 2:36)፡ በአንጻሩ አዳም ግን በምድር ኑሮው ለእግዚአብሔር አልታዘዘም (ቁርኣን 2:36)። ስለዚህም አዳም የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነው እንደ ኢየሱስ አንድ ዓይነት ባህርይ አልነበረውም።
የኢየሱስ ማንነት 

ስለዚህ እንደ ቁርኣን አባባል ኢየሱስ መንፈሳዊ ባህርይ አለው። ነገር ግን ኢየሱስ ሥጋ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ካልሆነ፡ ማለትም ክርስቲያኖች እንደሚያምኑት፡ ደግሞም ዝም ብሎ ሟች ካልሆነ፡ ታዲያ የኢየሱስ ማንነት ምንድነው? እዚህ ላይ በቁርአን ስለ ኢየሱስ ያለው ሙሉ ገለጻ ነው ብለን ልንደመድም እንችላለንን? የለም፡ እንደዛ አይመስልም። በቁርአን ውስጥ ተጨማሪ ተጨባጭ ነጥቦች አሉ።

ቁርኣን ከማንኛቸውም የታወቁ ሰዎች ይልቅ ለኢየሱስ የበለጠውን ከፍተኛ ስሞች ይሰጣል።
እርሱ ‘ታምር’ ነው (ቁርኣን 19:21፤ 21:91)፡ አንድ ‘ችሮታ’ ነው (ቁርኣን 19:21) ደግሞም ‘ተጠባባቂ‘ (ቁርኣን 4:171) ተብሏል።
በቁርአን ውስጥ ስለ ኢየሱስ ሁልጊዜ በአክብሮት ነው የሚነገረው።
በቁርአን ውስጥ በኢየሱስ ላይ የተሰነዘረ ነቀፌታ የለም።
በቁርአን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ሓዋርያ፡ የእግዚአብሔር ቃል (ካሊማ) እና የእግዚአብሔር መንፈስ (ሩህ) (ቁርኣን 4:171) ተብሎ ይጠራል።

በቁርአን ውስጥ ‘ባሻር‘ የተባለው የአረብኛ ቃል የሚያመለክተው የመናፍስትን ዓለም ሳይሆን አንድ ሟችን ነው የሚያመለክተው። ሙሐመድ ልክ እንደ ሌሎቹ ተራ ሰው ነው (ቁርኣን 18:110፤ 41:6)። ሌሎቹም ነቢያት ልክ እንደዚሁ ናቸው። ስለዚህም ባሻር የሚለው ቃል ኢየሱስን በተመለከተ አለመገኘቱ እንግዳ ነገር ነው። ኢየሱስ ተራ ሰው እንጂ አምላክ አለመሆኑ ይህ ዋና ማስረጃ ሊሆን ይችል ነበር። አሁን ይህን ጥያቄ በሚገባ ልንመለከተው ይገባል፡ ኢየሱስ ከነቢይ ያለፈ የነበረ ሊሆን ይችላልን? ቁርአን ስለ ኢየሱስ የሚለውን አስታውስ፡

ኢየሱስ የተወለደው ከድንግል ነው (ቁርኣን 19:20-22)።
ኢየሱስ ጉድለት የለውም (ቁርኣን 19-19)።
ኢየሱስ በሽተኞችን የሚፈውስ ታላቅ ፈዋሽ ነበር (ቁርኣን 3:49፤ 5:110)።
ኢየሱስ በእግዚአብሔር ወደ ሰማይ ተወሰደ (ቁርኣን 4:158)።
ኢየሱስ ተመልሶ ይመጣል (ቁርአን 3:45፤ 43:61)።

ደግሞም ይህ ብቻ አይደለም። በቁርኣን ስለ ኢየሱስ ሌላ ተጨማሪም አለ። ቁርኣን በእግዚአብሔር አገልጋዮች መካከል የተለየ ልዩነት እንዳለ ይታመናል (ቁርኣን 2:253)። በቁርኣን ውስጥ ኢየሱስ አንድ የተለየ ደረጃ ነው ያለው። ኢየሱስ ማሳመኛ የእግዚአብሔር መልክተኛ ነው (ቁርኣን 2:253፤ 43:63) ፤ ኢየሱስ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ድጋፍ አገኘ (ቁርኣን 2:253)። ኢየሱስ እጅግ በጣም የተከበረ ሰው ነው፡ በዚህኛው ዓለምም ሆነ በሌላኛው ዓለም (ቁርኣን 3:45)። ይህም ቅድስናና በረከቶች ማለት እንደሆነ የሚያብራሩ መጻሕፍት ሁሉ ይስማማሉ። [5]. ኢየሱስ ብቻ ነው ‘የመፍጠር‘ እና ‘ሕይወት የመስጠትን’ ድርጊቶች ሊያደርግ የሚችለው (ቁርኣን 3:49)። እንደዚህ ያሉትን ተግባሮች ያደረገ ነቢይ የለም። ስለዚህም የኢየሱስ ደረጃ ከሌሎቹ ሁሉ ከፍ ያለ ደረጃ ነው፤ ማንም ሰው ደርሶበት ወደ ማያውቀውም ደረጃ ከፍ ያደርገዋል። ስለ ኢየሱስ ምን ታስባለህ? እርሱ ዝም ብሎ እንደ ሌላ ነቢይ ነው ትላለህ?


 
ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት። እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:5)
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free