በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:15)
1BIBLE
በመጀመሪያ እግዚአብሔር.........................................

Bible Truth የእውነት ቃል


የሐዲስ
 ኪዳን  ካህናት

ሐዲስ ኪዳን ከአማኞች የተለዩ ካህናት እንዳሉ ይናገራልን?

በሐዲስ  ኪዳን  ከአማኞች  የተለዩ  ካህናት  አሉን?”  የሚለው  ጥያቄ መመለስ  ያለበት  ጥያቄ  ነው።  ምክንያቱም ትምህርተ  ሃይማኖትና  ክርስቲያናዊ ምግባር”  ጸሓፊና ሌሎችም፥  ዛሬ  የኢየሱስ ክርስቶስን  የክህነት  አገልግሎት ወክለውና  ተክተው  የሚሠሩና  ከምእመናን  የተለየ  ክህነት  ያላቸው  ካህናት  አሉ  የሚሉ  ወገኖች  አሉ።  ይህን ትምህርታቸውን  የሚደግፍ ጥቅስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባይኖርም፥ ስለ ሌሎች ጒዳዮች  የተነገሩትን ጥቅሶች በመጥቀስ  ሐሳባቸው  መጽሐፍ  ቅዱሳዊ  መሆኑን  ለማሳየት  ይሞክራሉ።  ለምሳሌ፥  ሊቀ  ጉባኤ  አባ  አበራ በመጽሐፋቸው  ያሰፈሩትንና  ከላይ  የጠቀስነውን  እዚህ  ላይ ብንመለከተው  ነገሩን ይበልጥ  ግልጽ  ያደርግልናል።በዐዲስ ኪዳንም ሥልጣነ ክህነት ለተመረጡት ብቻ እንጂ ለአማኞች ሁሉ ለሁሉ እንደማይሰጥና ለተመረጡት ብቻ እንጂ አማኞች ለሆኑት ሁሉ ለወንዶችም ለሴቶችም አይሰጥም። እንዲያማ ካልሆነ ክርስቶስ ከብዙዎች መካከል ለምን  ዐሥራ  ሁለቱን  ከዚያም  ሰባውን  ደቀ መዛሙርት  ብቻ መረጠሐዋርያው  ጳውሎስም  የክህነት  ሹመት ከመሰጠቱ  በፊት  በጥንቃቄ  እንዲሆን  በማሰብ መልካም ጠባያቸውንና  አኗኗራቸውን  በማስመልከት መመረጥና መሾም ስለሚገባቸው ካህናት መመሪያ አዘጋጅቷል  (1 ጢሞ. 31-13 ቲቶ  16-9) በዚህም ምክንያት ፈጥኖ እጆቹን በመጫን ካህናትን እንዳይሾም ጢሞቴዎስን አስጠንቅቆታል (1 ጢሞ. 522)” (ገጽ 260261)  ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ እና ለቲቶ በጻፋቸው መልእክቶች ውስጥ ያሰፈረውን ሐሳብ ከመልእክቶቹ ጥቂቱን በመጥቀስ እንመልከት። ለጢሞቴዎስ በጻፈው መልእክት ውስጥ፥ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል የሚለው ቃል የታመነ ነው። እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥  ራሱን  የሚገዛ፥  እንደሚገባው  የሚሠራ፥  እንግዳ  ተቀባይ፥  ለማስተማር  የሚበቃ፥  የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ፥ ነገር ግን ገር የሆነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥ ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፤ ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል?” ብሏል (1ጢሞ. 31-5) ለቲቶ  ደግሞ  እንዲህ  ሲል  ጽፎለታል፤  “ስለዚህ ምክንያት  የቀረውን  እንድታደራጅ  በየከተማውም፥  እኔ  አንተን እንዳዘዝሁ፥  ሽማግሌዎችን  እንድትሾም  በቀርጤስ  ተውሁህ፤  የማይነቀፍና  የአንዲት  ሚስት  ባል  የሚሆን፥ የሚያምኑም ልጆች ያሉት፥ ስለ መዳራትም ወይም ስለ አለመታዘዝ  የማይከሰስ ማንም ቢኖር፥ ሹመው። ኤጲስ ቆጶስ፥  እንደ  እግዚአብሔር  መጋቢ፥  የማይነቀፍ  ሊሆን  ይገባዋልና፤  የማይኰራ፥  የማይቈጣ፥  የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ፥ ነውረኛ ረብ የማይወድ፥ ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ጠንቃቃ፥ ጻድቅ፥ ቅዱስ፥ ራሱን የሚገዛ ይሁን፤ ሕይወት በሚገኝበት ትምህርት ደግሞ ሊመክር፥ ተቃዋሚዎቹንም ሊወቅሥ ይችል ዘንድ፥ እንደ ተማረው በታመነ ቃል ይጽና።”  (ቲቶ 15-9) እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ስለ ካህናት፥ ስለ ክህነት አገልግሎት አይናገሩም። ስለ ቤተ ክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች፥ ቤተ ክርስቲያንን ስለ መመገብና ስለ ማስተዳደር ይናገራሉ ነው የሚናገሩት። ይኸውም ኤጲስ ቆጶሳትና ዲያቆናት ለአገልግሎት ስለሚሾሙበት መስፈርትና ቤተ ክርስቲያንን ስለ መመገባቸውና ስለ ማገልገላቸው እንጂ፥ እነርሱ ክርስቶስን በመወከል ካህናት ሆነው መሥዋዕት በማቅረብ በክህነት ስለሚያገለግሉት የክህነት አገልግሎት አይደለም። በክፍሎቹም ውስጥ ኤጲስ ቆጶሳት፥ ሽማግሌዎች (ቀሳውስት) ዲያቆናት፥ የተባሉ መሪዎችና አገልጋዮች፤ ቤተ ክርስቲያንን ማደራጀት፥ ማስተዳደር፥ መመገብ የሚሉ አገልግሎቶች እንጂ፥ ክህነት፥ ካህናት፥ መሥዋዕት የሚል አንድም ቃል ወይም ሐሳብ  የለም። ክፍሎቹ  የሚናገሩት ቤተ ክርስቲያንን ስለ መመገብና  ስለ መምራት እንጂ፥ በክህነት ሥራ ኢየሱስ ክርስቶስን ወክሎ መሥዋዕት ስለ ማቅረብ አይደለም የተባለው ለዚህ ነው።  ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ምግባርጸሓፊ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስትን ሹመት እንደ ክህነት በመቊጠር፥  “በሐዲስ  ኪዳንም ሥልጣነ ክህነት  ለተመረጡት  ብቻ  እንጂ  አማኞች  ለሆኑት  ሁሉ  ለወንዶችም ለሴቶችም አይሰጥም”  (ገጽ 261) በማለት ዛሬም እንደ ኦሪቱ ዐይነት ያሉ ካህናት እንዳሉ አስመስለው ጽፈዋል። የኦሪት  ሊቃነ  ካህናትን  ዛሬ  “ካህናት”  እየተባሉ  ከሚጠሩ  ቀሳውስት  ጋር ማነጻጸር  ከተጀመረ፥  ቤተ መቅደሱና መሥዋዕቱም ወደ ንጽጽር መግባታቸው አይቀርም። ይህ ንጽጽሮሽና በሐዲስ ኪዳን ሥልጣነ ክህነት በተወሰኑ ሰዎች እጅ  ነው የሚገኘው የሚለው ሐሳብ፥ በትውፊት ሲሠራበት የቈየውን አሠራር ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ለማስጠጋት ታስቦ የተደረገ እንጂ፥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አለመሆኑ ግን ይታወቃል። ምክንያቱም፥

Ø  ክህነትን በተመለከተ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተነጻጸሩት አሮን እና ኢየሱስ ናቸው እንጂ አሮንና ተከታዮቹ የብሉይ ኪዳን ሊቃነ ካህናትና ሐዋርያት አይደሉም (ዕብ. 51-10 71-28) 

Ø  የብሉይ ኪዳን ቤተ መቅደስና ጌታ ያገለገለባት ሰማያዊት ቅድስተ ቅዱሳን እንጂ፥ የኦሪቱ መቅደስ ከሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ጋር አልተነጻጸሩም (ዕብ. 81-2 91-811-1224)

Ø  የብሉይ ኪዳን የእንስሳት መሥዋዕቶች ጌታ በሰማያዊቱ ቅድስተ ቅዱሳን ጋር ካቀረበው ክቡር ደሙ ጋር

እንጂ በኅብስትና በወይን ከተሰጠው ከጌታ ሥጋና ደም ጋር አልተነጻጸሩም (ዕብ. 99-1325-26 101-14)  ታዲያ  የኦሪት  ካህናትን  ከሐዋርያትና  በእነርሱ  እግር  ከተተኩት  የቤተ  ክርስቲያን  መጋቢዎች፥  አስተዳዳሪዎችና አገልጋዮች ጋር በክህነት አገልግሎት ማመሳሰል ከምን የመጣ ነው? ቢባል፥ ነገሩ ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለውና በትውፊት ሲሠራበት  የኖረውንና ቀሳውስትን  የተለዩ ካህናት ብሎ  የመቊጠርን ልማድ  የተከተለ  ነው ከማለት በቀር ሌላ ምላሽ የሚገኝለት አይመስልም። ኀጢአተኛውን ሰው ከቅዱስ እግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉን በራሱ ስለ ፈጸመና የቀረ አንዳች  ነገር ስለሌለ፥ የክህነት አገልግሎቱን በውክልና ለሌሎች አልሰጠም። እርሱም እንኳ ከዚህ በኋላ ስለ ኀጢአት መሥዋዕት ማቅረብ እንደሌለበት ተጽፏል (ዕብ. 727  926  1012141826)  ስለዚህ  አንድ  ጊዜ  ባቀረበው መሥዋዕት  በእርሱ  በኩል  አምነው  የሚመጡትን ያድናቸዋል (ዕብ. 59-10)

የሐዲስ ኪዳን ካህናት የሚያቀርቡት መሥዋዕት ምንድን ነው?

ኢየሱስ ክርስቶስ የሐዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት  ነው። እርሱ የጠራቸውና የመረጣቸው የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና መጋቢዎች ምእመናንም ሁሉ ደግሞ ካህናት ይባላሉ  (1ጴጥ. 29 ራእ. 16) ስለ ኀጢአት  የቀረበውን አንድና ፍጹም መሥዋዕት አንድ ጊዜ ያቀረበው ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ በመሆኑ፥ ይህን መሥዋዕት እርሱም ደግሞ አያቀርብም፤ ሌሎች እንዲያቀርቡም ውክልና አልሰጠም። ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን በመሠዋት አንድ ጊዜ ካቀረበው ፍጹም መሥዋዕት ሌላም፥ ስለ ኀጢአት የሚቀርብ መሥዋዕት አለ ብሎ የሚያምንና የሚያስተምር ቢኖር የክርስቶስ ሊቀ ካህናትነት አልጠቀመም፤ መሥዋዕቱም በቂ አይደለም ማለቱ ነው።       ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ምግባርጸሓፊ የቤተ ክርስቲያን ቀሳውስትን ሹመት እንደ ክህነት በመቊጠር፥ ዛሬ እየሰጡ ያለውን መቅደሳዊ አገልግሎትም ከኦሪቱ የደብተራ ኦሪት የክህነት አገልግሎት ጋር በማመሳሰል፥ካህናተ ኦሪት የእንስሳት መሥዋዕትን ያቀርቡ ነበር። ካህናተ ወንጌል ግን እጅግ የላቀውንና የተቀደሰውን የጌታን ሥጋና ደም መሥዋዕት  የሚያቀርቡ ሆነዋል”  (ገጽ  259) ሲሉ ጽፈዋል። ይህን ንጽጽር ላይ ላዩን ለተመለከተው  የሚያስኬድ ይመስላል። ከላይ እንደ አየነው በማደሪያው ድንኳን መሥዋዕተ ኦሪትን ይሠዉ የነበሩት ሊቃነ ካህናት የሚነጻጸሩት ከክርስቶስ ጋር እንጂ ከሐዋርያት ጋር ባለመሆኑ ትምህርቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አለመሆኑ ይታወቃል።  የሐዲስ ኪዳን ካህናት የተባሉት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች፥ መጋቢዎችና ምእመናን በአጠቃላይ ይነጻጸሩ ከተባለም፥ ሊነጻጸሩ የሚችሉት በኦሪት፥  “አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ፤ እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ።” (ዘፀ. 195-6) ከተባሉት ሕዝበ እስራኤል ጋር ነው። ምክንያቱም በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ለክርስቲያኖች (አገልጋዮችና ምእመናን) ተመሳሳይ ይዘት ያለው ቃል ተነግሮላቸዋል፤እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤” (1ጴጥ. 29) እዚህ ላይ ሐዋርያው ጴጥሮስ ራሱንየንጉሥ ካህናትካላቸው ምእመናነ ወንጌል መካከል አላካተተምና  ጥቅሱ  “የተለየ  ክህነት  አላቸው”  ብለው  የተናገሩላቸውን  ሐዋርያትን  አይጨምርም  የሚሉ  ሊኖሩ ይችላሉ። ነገር ግን ሐዋርያው ዮሐንስ በራእዩ፥ለወደደን ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥ መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኀይል ይሁን፤ አሜን።በማለት፥ እርሱን ጨምሮ በክርስቶስ ደም ከኀጢአታቸው የታጠቡ ሁሉ ካህናት መሆናቸውን ጽፏል (15-6) ስለ ሐዲስ ኪዳን ካህናት፥እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።ተብሎ ተጽፏል  (1ጴጥ. 25)  ከዚህም  ካህናተ ወንጌል፥  በኢየሱስ  ክርስቶስ  በኩል  ለእግዚአብሔር  የሚያቀርቡት  ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕት እንዳለ እንረዳለን። መሥዋዕቱ ስለ ኀጢአት ስርየት የሚቀርብ መሥዋዕት፥ እንደ ትምህርተ  ሃይማኖትና  ክርስቲያናዊ  ምግባር”  ጸሓፊ  አመለካከትም  ሥጋ  ወደሙም   ሳይሆን፥  “መንፈሳዊ መሥዋዕትተብሏል።  መንፈሳዊ የተባለው መሥዋዕት ልዩ ልዩ ነው። እነዚህ መሥዋዕቶች ከኦሪቱ የእንስሳት መሥዋዕት የተለዩና ከእነርሱ ጋር ሲነጻጸሩ በእጅጉ በእግዚአብሔር የተወደዱ መሆናቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከቀረበው ንጽጽር መረዳት እንችላለን፤ 

Ø    ከሚቃጠልና ከሚታረድ መሥዋዕት ይልቅ የእግዚአብሔርን ቃል መስማት (1ሳሙ. 1522)    ከሚቃጠለው መሥዋዕት ይልቅ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ (መዝ. 5116-17) 

Ø    ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ቅን ነገርን ማድረግ (ምሳ. 213) 

Ø    ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን፥ ከሚቃጠልም መሥዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማወቅ (ሆሴ. 66) 

Ø    ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን (ማቴ. 913)  እግዚአብሔር እንደሚወድና መንፈሳዊው መሥዋዕት ከሚቃጠል መሥዋዕት እንደሚበልጥ በተደጋጋሚ ተናግሯል።

መንፈሳዊ መሥዋዕት የተባሉትም የሚከተሉት ናቸው። 

Ø    ሁለንተናን ሕያው መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ማቅረብ (ሮሜ 121-2 ኤፌ. 52)

Ø    ወንጌልን  ላልሰሙትና  ላላመኑት መመስከርና  በክርስቶስ  እንዲያምኑ፥  እንዲድኑና  ለክርስቶስም  ሕያዋን መሥዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ እንደካህን ማገልገል (ሮሜ 1515-16 1ጴጥ. 29-10)

Ø    የምስጋናን መሥዋዕት ማቅረብ (መዝ. 501423 546 10721-22 ዕብ. 1315)

Ø    መልካም ማድረግና ካለው ነገር ላይ ለሌሎች ማካፈል (ምሳ. 213 ፊል. 418 ዕብ. 1315)

Ø    ቃሉን የማድመጥና የመታዘዝ መሥዋዕት (1ሳሙ. 1522) (ጮራ ቊጥር 23 ገጽ 47 ይመልከቱ)

በሐዲስ ኪዳን ካህናት የሚቀርቡት መንፈሳውያን መሥዋዕቶች ከላይ የተዘረዘሩት ናቸው። ከእነዚህና ከመሳሰሉት በቀር  ስለ  ስርየተ  ኀጢአት  የሚቀርቡ  ሌሎች  መሥዋዕቶች  የሉም።  ሥጋ  ወደሙ  በትውፊታዊው  አስተምህሮመሥዋዕት”  ተብሎ  ቢጠራም፥  ስያሜው  መጽሐፍ  ቅዱሳዊ  መሠረት  የለውም፤  መሥዋዕት  ነው  መባሉም አመክንዮኣዊ አይደለም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አርብ ሊሰቀል ኀሙስ ማታ፥ በኅብስትና በወይን ሥጋውንና ደሙን እንዲቀበሉ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጥቷል፤ እንዲህ በማለት፥ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው፤ ጽዋውንም አንሥቶ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ስለ ብዙዎች ለኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የዐዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።” (ማቴ 2626-28) ከዚሁ ጋር አያይዞ፥  “ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉትብሏል  (ሉቃ. 2219  1ቆሮ. 1124) ከዚህ ውጪ ሥጋ ወደሙን  (ኅብስትና ወይኑን) መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር አላቀረበውም። ለእግዚአብሔር ያቀረበው ራሱን ነው (ኤፌ. 52 ዕብ. 727 91228) እኛን ለማዳን አንድ ጊዜ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ማቅረቡን ለማሰብና መታሰቢያውን ለማድረግ፥ ቤተ ክርስቲያን ምስጢረ ቊርባንን በመፈጸም የክርስቶስን መታሰቢያ ስታደርግ ኖራለች፤ ጌታ እስኪመጣ ድረስም መታሰቢያውን ታደርጋለች (.. 246  1ቆሮ. 1016-17 1120-34) ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ይህን ምስጢር በማዘጋጀታቸውና ለምእመናን በማቅረባቸው ከኦሪት የበለጠ መሥዋዕት አቀረቡ አያሰኛቸውም።


 
ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት። እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:5)
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free