በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:15)
1BIBLE
በመጀመሪያ እግዚአብሔር.........................................

ጥያቄዎቻችሁ

1. መዳን የሚገኘው በእምነት ነው ወይስ መልካም ሥራን በመሥራት ነው?

መልስ

መዳን የሚገኘው በእምነት መሆኑን በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ይናገራሉ፤ ጥቂቶቹም እንደሚከተለው ተጠቅሰዋል፡፡

  • «በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቊጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም» /ዮሐ.3፡36/፡፡
  • «ኢየሱስም መለሰ አላቸውም ... እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው»/ዮሐ.6፡47/፡፡
  • «በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህም ትድናላችሁ» /የሐ.ሥ.16፡31/፡፡
  • «አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጧል፤ እርሱም ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው»/ሮሜ3፡21‐22/፡፡
  • «መጽሐፍም እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አይቶ በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ» /ገላ.3፡8/፡፡
  • «የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታወቁ ዘንደ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ» /1ዮሐ.5፡13/፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ መዳን የሚገኘው በእምነት መሆኑን የሚገልጸውን ያህል በሥራ እንደማይገኝም በአጽንኦት ይናገራል፤ ይህንንም በሚከተሉት ጥቅሶች ውስጥ እናያለን፡፡

  • «ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቈጥራለንና» /ሮሜ3፡28/
  • «... ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል» /ገላ.2፡16/፡፡
  • ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሏልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው» /ገላ.3፡11/፡፡
  • «ጸጋው በእምነት አድኗችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም» /ኤፌ.2፡8/፡፡
  • «... ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለነበረው ሥራ አይደለም»/ቲቶ 3፡4‐5/፡፡

ስለዚህ ከእነዚህ ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መዳን የሚገኘው በእምነት እንጂ በሥራ እንዳልሆነ በግልጽ እንማራለን፡፡

www.ewnet.org.et/btm_files/FAQ0.htm

 


 
ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት። እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:5)
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free