በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:15)
1BIBLE
በመጀመሪያ እግዚአብሔር.........................................

ቤተ እምነት Denomination

ቤተ እምነት (Denomination)ማለትምን ማለት ነው?


                           የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የጋራ ለሆነ እምነትና አምልኮ የተሰበሰቡትና የተደራጁበት ተቋም ነው፡፡ አንድ ዲኖሚኔሽን የሚከተሉትን መታወቂያዎች ይይዛል፡-
1. መጠሪያ ሥም
ቤተክርስቲያንን በተመለከተ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ ፣ እንግሊካን፣ ፕሪስቢቴሪያን፣ ባብቲስት፣ ሉትራን ፣ ሙሉወንጌል ወዘተ….. የሚሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተሰጡ ስያሜዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ቤተክርስቲያንን ሲሰይም በቦታው (አጥቢያው) መጠሪያ ወይም ስም ብቻና ብቻ ነው፡፡ የቆሮንጦስ ቤተክርስቲያን፣የፊልደልፊያ፣ የሮም፣ የቆላስያስ፣ የተሰሎንቄ፣ የኤፌሶን ወዘተ….. እያሉ አውራጃ ከሆነ ደግሞ የገላትያ፣ የአካይያ አብያተ ክርስቲያናት እያለ ሰይሞአል፡፡ ከዚህ ሥያሜ ውጭ ያለው ወደ ዲኖሚኔሽን ይመራል፡፡
2. የእምነት መግለጫ
የጉባኤዎች ወይም የዲኖሚኔሽኑ ሊሆን ይችላል፡፡
3. ዶክትሪን
ያለፉ የቤተክርስቲያን አባቶች ወይም የዲኖሚኔሽን ሊሆን ይችላል፡፡
የቤተክርስቲያን ዋናው የእምነት መግለጫም ሆነ ዶክትሪን መፅሐፍ ቅዱስ በተለይም አዲስ ኪዳን ነው መሆን ያለበት፡፡ ትክክለኛውን አተረጓጎም ለማግኘት ግን በግልም ሆነ በጉባኤ ጥናት ወዳለፉት አባቶች ሄዶ ማጣቀስም ሆነ መታረም ተገቢ ይሆናል፡፡
4. መተዳደሪያ ደንብ
ይህ ያስፈለገው ዲኖሚኔሽንዋን ለመጠበቅና በሰዋዊ ጥበብ ሥራዋን ለማቀላጠፍ ነው፡፡ ግን መፅሐፍ ቅዱስና መንፈስ ቅዱስ የሚያስቀምጡልንን መንገድ መጠቀም ይበጃል፡፡
መንግስትም ለምዝገባ መተዳደራያ ደንብ ይፈልጋል፡፡ መፅሐፍ ቅዱስን ገልብጦ መስጠት ነው፡፡
5. የአስተዳደር መዋቅር
በተቻለ መጠን መፅሐፍ ቅዱሳዊ ማድረግ ይበጃል፡፡ የከተማዋ ቤተክርስቲያን ባልተከፈለ አመራር ትተዳደራለች፣ሽማግሌዎችና ሐዋርያት፣ እረኞች፣ ወንጌላውያን፣ አስተማሪዎችና ነቢያት የተቀናጁበት አመራር አስፈላጊ ነው፡፡ አመራሩ በመፅሐፍ ቅዱስና በመንፈስ ቅዱስ ሥር መሆን ይገባዋል፡፡
6. የፍቃድ ወረቀት
እነዚህ ሁሉ አንድን የአምልኮ ማህበር ዲኒሚኔሽን ያሰኙታል፡፡ ለጥንቱዋ ቤተክርስቲያን ግን 
ሀ. በአካባቢው ሥም የተሰየመ መጠሪያ ብቻ ነበራት፡፡
ለ. የእምነት መግለጫ፣ ዶክትሪንዋና መተዳደሪያ ደንቡዋ መጽሐፍ ቅዱስ እና የመንፈስ 
ምሪት ነበሩ፡፡
ሐ. ያልተወሳሰበ አስተዳደር ነበራት፡፡
መ. ፍቃድ ወረቀት ከመንግስት አላስፈለጋትም፡፡
ስለዚህ አጥቢያዊት እንጂ ቤተእምነታዊት (denominational) አልነበረችም፡፡
ስለዚህ ይህንን ዲኖሚኔሽናዊ (ቤተእምነታዊ) ወጥመድ በማምለጥ እንዴት ወንጌል መስራት ይቻላል የእገሊት ቤተክርስቲያን ብለን ብንደራጅ የቦታውንም ሥም ብትጨምርበት ያው ዲኖሚኔሽን መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ 
ለምሳሌ የሐረር ወንጌላዊነት ቤተክርስቲያን ቢባልም ያው ነው፡፡ የሐረር የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ቢባልም በአሁኑ ወቅት እንኩዋ ከሁለት አስርት በላይ ከሚቆጠሩት ቤተእምነቶች አንዱዋ መሆን ነው፡፡
ስለዚህ የጌታ ተከታዮች በአንፆኪያ ባለመኑት ሰዎች ክርስቲያን ከመባላቸው በፊት በጌታ ወደ ተጠሩበት ሥያሜ መመለስ ያሻል:: ያውም ደቀመዛሙርት (disciples ) ነው፡፡ ጌታ የጠራቸው በዋነኝነት በዚህ ሥያሜ ነው፡፡ ስለዚህ በሐረር ያሉ፣ በአዲስ አበባ ያሉ ፣ በደሴ ያሉ የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ወዘተ…. በማለት በአካባቢው ሥም መጥራት ይመረጣል፡፡
መተዳደሪያ ደንብን በተመለከተ በመንግስት አስገዳጅ ከሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተገለበጠ ነገር መስጠት ይመረጣል፡፡ አብሮ አምስቱን የአገልግሎት ስጦታዎችና ሽማግሌዎችን ያካተተ መፅሐፍ ቅዱሳዊ የከተማ አጥቢያዊ የአስተዳደር አወቃቀር አብሮ መስጠትም ይቻላል፡፡

ዶክትሪን እና የእምነት መግለጫ ግን ያው መፅሐፍ ቅዱስ በተለይም አዲስ ኪዳን ይሆናል፡፡ ለትክክለኛ አተረጓጎም ወደ አባቶች ዘወር ብሎ ማጣቀስ ግድ ይላል፡፡
ዋናው ነገር ከዶክትሪን ከእምነት መግለጫ እና ሥያሜ መጠበቅ ነው፡፡ እነዚህ ናቸው በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ድርጅታዊ ክፍፍል ወቅት ሚና የተጫወቱትና ለዛሬው ለቁጥር የሚያታክቱ ቤተእምነቶች መፈልፈል መሠረት የጣሉት፡፡

ልዩነት በከሰት እንኩዋ የዶግማ ፣ የዶክትሪን ወይስ የአመለካከት? ብሎ መመርመር ይገባል፡፡ የዶግማ (dogma) ከሆነ ከድነት ጋር ስለሚያያዝ ወደ ክህደት (apostasy) ያመራር፡፡ ዶክትሪን (doctrine) ከሆነ ልዩነቱ ከድነት ጋር አይያያዝም ግን ኑፋቄ (heresy ) ነው፡፡ አመለካከት (opinion) ግን የትርጓሜ (Interpretation) ልዩነት ስለሆነ ምንም አይደለም፡፡ ዛሬ ቤተእምነቶች እንደህ የተከፋፈሉትና የተፈለፈሉት በዶግማ ልዩነት ሳይሆን በዶክትሪን እና በአመለካከት ልዩነት ላይ በመመሥረት ነው፡፡ ይህ መፅሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፡፡ ቤተክርስቲያን የምትመሠረተው በአለቱ በክርስቶስ ላይ እና ስለእርሱ ሐዋርያትና ነቢያት ባስቀመጡት የዶክትሪን መሠረት ላይ ብቻ ነው፡፡


 
ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት። እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:5)
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free