በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:15)
1BIBLE
በመጀመሪያ እግዚአብሔር.........................................

መጽሐፍ ቅዱስ እና ታቦት

 


ታቦት ማለት
ጽላት የሚቀመጥበት ሳጥን ማለት ነው ጥሬ ትርጉሙ ማደሪያ የሚል ነው የጽላት ማደሪያ ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል። መጽሐፍ ቅዱስ ታቦት የሚለው ምን ዓይነት እንደሆነ ዘጸ. 25፥10-22 የተጻፈውን መረጃ በማድረግ ምስሉን ጨምር እናሳያችሁ። ከላይ በጠቀስነው የእግዚአብሔር ቃል መሠረት ታቦት ከግራር እንጨት የሚሠራና በወርቅ የተለበጠ ትልቅ እቃ ነው።

1. ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣
ቁመቱ አንድ ክንድ ተኩል፣
ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል ነው።
ታቦቱ አንድ ብቻ ነው

2. በውስጥና በውጭ በወርቅ የተለበጠ፣
ዙሪያውን የወርቅ አክሊል ያለው፣
አራት እግሮች ያሉት 
አራት ቀለበቶች ያሉት
ሁለት መሎጊያዎች(መሸከሚያዎች)ያሉት ነው።

3. በላዩ ላይ ሁለት ክንድ ተኩል የሆነ የሥርየት መክደኛ ያለው፣
በላይና በታች በዚህና በዚያ ሁለት ኪሮቤል ያለው፣
ስያሜው የቃል ኪዳኑ ታቦት ተብሎ ይጠራል።

ጽላት
አሠርቱ ትእዛዛት በሁለት ወገን የተጻፉባቸው ሁለት ድንጋዮች ናቸው፤ ሁለቱም ጽላቶች ከላይ በተገለጠው ታቦት ውስጥ ይቀመጣሉ። ከቶ ከዚያ አይወጡም። ዘጸ 32፥15

አገልግሎቱ
ሁለቱን ድንጋዮች ለማስቀመጥ የሚያገለገል ሲሆን፣ በብሉይ ኪዳን ዘመን የሚሠዉ የእንሥሳት ደም በታቦቱ ላይ ባለው የሥርዬት መክደኛ ላይ ይረጭ ነበር። በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ደመና ይታይ ስለነበር እግዚአብሔርም በሕጉ ላይ ሆኖ ይናገር ነበር።

ስለ ታቦት እና ስለ ጽላት ከላይ ያየነው መግለጫ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው የተደረገ ነው። "እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ጽላቱን ወስዶ በታቦቱ ዘንድ አኖረ” ዘጸ 40፥20 "ጽላቶችንም በሠራሁት ታቦት ውስጥ አደርግኋቸው እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ በዚያ ኖሩ” ዘዳ 10፥5። እግዚአብሔር ይህን ትእዛዝ ለሙሴ ሲሰጥ እንዲህ አስጠንቅቆት ነበር "እኔ ያዘዝኋችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትጠብቃላችሁ እንጂ ባዘዝኋችሁ ቃል ላይ አትጨምሩም ከእርሱም አታጎድሉም” ዘዳ 4፥2-3።

ታቦት እንደዚህ በእግዚአብሔር ትእዛዝ የተሠራ ከሆነአሁን በኢትዮጵያ ያለውን ታቦት ምን ልንለው ነው? በእግዚአብሔር ትእዛዝ የተሠራ ነውን?

ይህን መልስ ከመመላሳችን በፊት ስለ ኢትዮጵያ ታቦት አሠራር ከምስሉ ጋር እናሳያችሁ ከዚያ በመጽሐፍ ቅዱስ ከታዘዘው ታቦት ጋር አስተያዩና ፍርዳችሁን ስጡ።

የኢትዮጵያ ታቦት

1. ልኩና መጠኑ ብዛቱና ዓይነቱ ተለይቶ አይታወቅም፤
ከዋንዛ፣ ከወይራ፣ ወይም ሌላ ጠንከር ካለ እንጨት ሊሠራ ይችላል፣
በአሁኑ ሰዓት ከመቶ በላይ ታቦት ሊኖር ይችላል፤
ዙሪያውን ሐረግ ጥልፍ የመሰለ ሐረግ ይቀረጽበታል።

2. ስያሜው የማርያም፣ የሚካኤል፣ የገብርኤል ወዘተ ይባላል
በላዩ ላይ የሀገሩ ስም ተጽፎበታል ለምሳሌ የሰበታ ከሆነ ሰበታ ገብሬል ይላ
ዝቅ ብሎ የደብሩ አስተዳድሪ ወይም ቄሰ ገበዝ ስም ይጻፍበታል፣
ታቦቱ የተሰየመበት ሰው ስእል ይቀረጽበታል፣ ካላይ የሥላሴ ከታች የጻድቁ
3. በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ጽላት ወይም ታቦት ሊባል አይችልም፤
ጽላት እንዳይባል ከድንጋይ የተሠራ አይደለም፤ ከንጨትም ይሠራል፣
አሠርቱ ትእዛዝትም አልተጻፈበትም፣ ስእል ግን አለበት፣
ታቦት እንዳይባል እንደ ሳጥን የተሠራ አይደለም፤
እግዚአብሔር ካዘዘው ታቦት ጋር ብናስተያየው አንዱንም ቃል አያሟላም

4. አንዳድ ታቦቶች አልፋ ኦሜጋ የሚል ተጽፎባቸዋል፣ 
አንዳዶች ግን ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይንበርከክ የሚል ተጽፎበታል
አንዳዶች ምንም አልተጻፈባችውም እንዲሁ የሰው ሙያ ይታይባቸዋል።

5. ስለኢትዮጵያው ታቦት አሠራር በሔትኛውም መጽሐፍ አልታዘዘም፤
መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ፈጽሞ የማናገኘው ሲሆን አዋልድ በሚባሉ መጽሕፍት ላይም ስለ አሠራሩ የተደነገጉ ሕጎች አላገኘንም እንኳንስ በእግዚአብሔር ትዛዝ የሰውም ትእዛዝልናገኘን አላቻልንም፣ ስለዚህ ማንም እንደየሙያው የሚሠራው ሆኖ አግኝተነዋል። የመጽሐፍ ቅዱሱ ታቦት በሙሴ አንድ ጊዜ ብቻ የተሠራ ሲሆን የኢትዮጵያው ታቦት ግን ሙያ ያለው ሁሉ በፈለገ ጊዜ ሊሠራው የሚችል ነው ለምሳሌ እኔ ከ10 በላይ ታቦት እየሠሩ የሚሸጡ ሰዎችን አውቃለሁ የሁሉም ሥራ እንደየችሎታቸው የተለያየ ነው።

ታዲያ የኢትዮጵያ ታቦት፤ ታቦትም ካልሆነ ጽላትም ካልሆነ ምን እንበለው ይሆን? አንዳዶች ለጊዜው ማምለጫ ይሆናል ያሉትን ትምህርት አዘጋጅተዋልለምሳሌ፣ የቅዱሳን መታሰቢያ ነው የሚሉ አሉ። ሥጋውና ደሙን ለመፈተት የምንጠቀምበት ገበታ ነው የሚሉም አሉ ይህ አባባል ትንሽ የሚያስመልጥ ይመስላል። እኛ ግን በጥንት ዘመን ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት ይሰጥ የነበረ መታወቂያ ወይም የፈቃድ ወረቀት ሠርተፊኬት ነበረ እንላልን። ማስረጃችንም በጽላቱ ላይ የተጻፈው የቄሰ ገበዙ ስም፣ የቦታው ወይም የደብሩ ስም፣ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያኑ የተሰየመበት ቅዱስ ስም ነው። ይህ የሚያመለክተው ቤተ ክርስቲያን ለማቋቋም የተሰጠ ፈቅድ መሆኑን እንጂ በእርግጥ እንደ እግዚአብሔር ቃል የተሥራ ሆኖ ሊሰገድለት የሚገባ ነገር አይደለም።


 
ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት። እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:5)
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free