የማርያም አባት ማን ነበር?
የማርያም አባት ማን ነበር? የማርያም አባት በማቴዎስ 1.16 መሰረት ያዕቆብ ነበር ወይንስ በሉቃስ 3.23 ላይ እንዳለው ኤሊ ነበር?
ለዚህ ጥያቄ ያለው መልስ በጣም ቀላል ነው ነገር ግን ገለፃን ይፈልጋል፡፡ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች በአሁኑ ጊዜ የሚስማሙት ማቴዎስ የሰጠው የዮሴፍን ዘር ሲሆን ሉቃስ ደግሞ የሰጠው የማርያምን ዘር በመሆኑ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ያዕቆብን ያደረጉት የዮሴፍ አባት ሲሆን ኤሊን ደግሞ ያደረጉት የማርያም አባት ነው፡፡
ይህ የሚታየው በሁለቱ የድንግል መውለድ ታሪኮች ውስጥ ነው በማቴዎስ 1.18-25 ላይ ያለው ታሪክ ያተኮረው በዮሴፍ ሁኔታ ላይ ነው፣ ሉቃስ 11.26-56 ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ከማርያም አኳያ የተነሳ ነው፡፡
ለመጠየቅ ሎጂካዊ ጥያቄ የሚሆነው በሁለቱም ትውልድ ሀረጎች ላይ ዮሴፍ ስለምን ተጠቀሰ? የሚለው ነው፡፡ መልሱም እንደገና በጣም ቀላል ነው፡፡ ሉቃስ የተከተለው በጣም ጥብቅ የሆነ የዕብራይስጥን ባህል ሲሆን በዚያም የጠቀሰው ወንዶችን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም በዚህ ጉዳይ ላይ ማርያም እዚህ ላይ የተገለጠችው በባሏ ስም ነው፡፡ ይህ አመለካከት በሁለት የማስረጃ ነጥቦች የተደገፈ ነው፡፡ በመጀመሪያ በግሪኩ የሉቃስ ጽሑፍ ላይ እያንዳንዱ ስም ከስሞቹ ቀድሞ “አርቲክል” አላቸው ለምሳሌም ያህል (የኤሊ the Heli, የማታት the Matthat) ይላል፡፡ በዮሴፍ ላይ ግን አርቲክሉ የለም ስለዚህም የዮሴፍ ስም አጻጻፍ ከሌሎቹ የተለየ ነው፡፡ ይህ እውነታ በእንግሊዝኛውም በአማርኛውም ላይ ግልጥ አይደለም በመጀመሪያው የግሪኩ ቋንቋ ላይ ግን ግልጥ ነው፡፡ ይህም ግሪክን የሚያነብ ማንንም ሰው የሚያስደንቅ ነው የሚሆነው፣ ይህም አጻጻፉ የሚያሳየው የዮሴፍን ሚስት ዘር ግንድ ነው፡፡ ምንም እንኳን የእርሱ የዮሴፍ ስም ቢጠቀስም ለመናገር የታቀደው ግን የማርያምን ዘር ነው፡፡ ሁለተኛው የማስረጃ መስመር ያለው የአይሁድ ምንጭ በሆነው በኢየሩሳሌሙ ታልሙድ ላይ ነው፡፡ ይህም የዘር ትውልዱ የማርያም መሆኑን ያሳያል፣ እርሷን የኤሌ ልጅ እንደሆነች መዝግቧል፡፡ (ሃጊጋ 2.4)