ኢየሱስን ጌታ
አዲስ ኪዳን ኢየሱስን ጌታ ብሎ ሲጠራው፣ ኪዩሪየስ (Kurios) የተሰኘውን የግሪክ ቃል ፍቺ ይይዛል፡፡ ኪዩሪየስ (Kurios) ገዢ ወይንም ጌታ የሚለውን የተለመደ ቃል ፍቺ ይይዛል፣ ይህም የእንግሊዝኛው ቃል ጌታዬ (Sir) በማለት አገልግሎት ላይ የሚያውለውን የአክብሮት መጠሪያም ይዞ ያገለግላል፡፡ ለነገሩ፣ ኪዩሪየስ የሚለው ቃል በተደጋጋሚ ጊዜ ለሰብዓዊ ሰዎችም አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ ይህንንም በማቴዎስ ምዕራፍ 10 ቁጥር 24፣ ሉቃስ ምዕራፍ 12 ከቁጥር 36 እስከ 47፣ ኤፌሶን ምዕራፍ 6 ከቁጥር 5 እስከ 9 እና በሌሎችም በርካታ ስፍራዎች እናገኘዋለን፡፡ በተመሳሳይም፣ አዲስ ኪዳን ኪዩሪየስ የሚለውን ቃል የእግዚአብሔር ስም አድርጎም ተጠቅሞበታል፡፡ ይህንንም በማቴዎስ ምዕራፍ 11 ቁጥር 25፣ ሉቃስ ምዕራፍ 1 ቁጥር 16፣ የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 ቁጥር 39 እና በሌሎችም በርካታ ምንባቦች እናገኘዋለን፡፡ ይህንን ሰፊ አፈታት ከተመለከትን፣ በአዲስ ኪዳን ኪዩሪየስ የሚለው ቃል የኢየሱስን መለኮትነት ያመለክታል ብለን ለምን እናስባለን? ለምንድን ነው ቃሉ በምድር ያለውን ሥልጣንና ክብር ብቻ ለማመልከት የማንጠቀምበት? ብለን መጠየቅ መልካም ነው፡፡ የክርስቲያኖች ኪዩሪየስ የሚለው ቃል አጠቃቀም ቁልፉ ብሉይ ኪዳን ነው፡፡ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት የተጻፉት በዕብራይስጥ ነው፡፡ ሆኖም፣ ክርስቶስ ከመወለዱ ጥቂት ምዕተ-ዓመታት ቀደም ብሎ፣ የዕብራይስጡ ቅጂ ወደ ግሪክ ተተረጎመ፡፡ ይህም ትርጉም Septuagint ሰብዓ ሊቃናት በሚል መጠሪያ ይታወቃል፡፡ የአይሁድ ምሁራን ብሉይ ኪዳንን ወደ ግሪክ ሲተረጉሙ፣ ኪዩሪየስ የሚለውን የግሪክ ቃል 6700 ጊዜ ያህል እግዚአብሔር ለህዝቡ ራሱን የገለጠበትን ያህዌ (Yahweh) የተሰኘ ቅዱስ ስም ለመተርጎም ተጠቅመውበታል፡፡ ይህ የቀደምት ታሪክ ማስታወሻ አዲስ ኪዳን ለኢየሱስ ያዋለውን የኪዩሪየስ ፍቺ ለመረዳት ወሳኝ ሚና አለው፡፡ ምንም እንኳን ኪዩሪየስ የሚለው ቃል በራሱ የኢየሱስን መለኮትነት ባያስረዳም፣ የዚህ ቃል የብሉይ ኪዳን ቀደምት ታሪክ ማስታወሻ በርካታ ምንባቦች ውስጥ የኢየሱስን መለኮትነት በግልጥ እንዲያመለክት አድርጎታል፡፡ በአዲስ ኪዳን ከምናገኛቸው አስደናቂ ምንባቦች አንዱ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ (ፊልጵስዩስ 2፥10-11) በመሠረቱ፣ ጳውሎስ፣ በዚያን ወቅት የጠቀሰው ከኢሳያስ ነው፣ ያም ያህዌ ጌታ ነው ብሎ እያንዳንዱ ሰው የሚያውጅ መሆኑን የሚገልጥ ዝማሬ ነው፡፡ እርሱም ን ብሎ የብሉይ ኪዳኑን ምንባብ ወስዶ ያንኑ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው ብሎ ተጠቅሞበታል፡፡ በዚያም ወቅት አዲስ ኪዳን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያው ምድራዊ ጌታ ብቻ ሳይሆን፣ ከእስራኤል ጌታ አምላክ ጋር አንድ እንደሆነ በግልጽ ያመለክት እንደነበር እውቅ ነበር፡፡ እስኪ ጳውሎስ በሮሜ ምዕራፍ 10 ቁጥር 9እና 13 ላይ የጻፈውን አድምጡ፡ ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤… የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና። በቁጥር 13 ላይ ጳውሎስ የሚያጣቅሰው ከኢዩኤል ምዕራፍ 2 ቁጥር 32 ሲሆን ይህንንም የኢየሱስን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል የሚለውን ለማረጋገጥ ተጠቅሞበታል፡፡ ከኢዩኤል የተጠቀሰው ጥቅስ በብሉይ ኪዳን፣ ጌታ የሚለው ስም ያህዌ፣ አግባብነት ያለው የእግዚአብሔር ስም መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ በቀላሉ ስናስቀምጠውም፣ ጳውሎስ ኢየሱስ ጌታ ነው ሲል፣ ኢየሱስ ያህዌ፣ የብሉይ ኪዳኑ ጌታና አምላክ ነው ማለቱ ነው፡፡ኢየሱስን ከብሉይ ኪዳኑ አምላክ ጋር የሚያስተካክሉት የአዲሰ ኪዳን ምንባቦች ማቴዎስ ምዕራፍ 3፣ ማርቆስ ምዕራፍ 1፣ ሉቃስ ምዕራፍ 3 እና ዮሐንስ ምዕራፍ 1 ሲሆኑ በዚያም ኢየሱስ በኢሳያስ ምዕራፍ 40 የተጠቀሰውና መጥምቁ ዮሐንስም መንገዱን የጠረገለት ጌታ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ተመሳሳዩን መግለጫ በዕብራውያን ምዕራፍ 1 ቁጥር 10 ላይ ጌታ ኢየሱስ በመዝሙር 102 ከቁጥር 24 -25 ዓለምን የፈጠረ ተብሎ የተጠቀሰው ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ዝርዝሩ እንዲህ እንዲህ እያለ ይቀጥላል፡፡ እንግዲህ፣ በአዲስ ኪዳን ሰዎች ኢየሱስን “ጌታ” ሲሉት ዘወትር መለኮትንቱን ማመልከታቸው ነው እያልን አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰብዓዊ ከበሬታን ሊሰጡትም ሲሹ ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ነገር ግን ቤተክርስቲያን ልክ እኛ በሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ እንደምናደርገው ስታውጅ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ፣ በአምላክነቱም የስላሴ ምሉዕ አባል፣ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ እኩል መለኮታዊ የባህርይ መገለጫዎች ያሉት ነው የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ማረጋገጣችን ነው፡፡ የክርስቶስ መለኮትነት ለክርስትና ሕይወት ሁሉን ዓይነት እንድምታ አካትቷል፡፡ ለምሳሌ፣ በጸሎቶቻችንና በዝማሬዎቻችን ሁሉ ኢየሱስን እንደ አምላክ ልናመልከውና እውቅና ልንሰጥ የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ ትምህርት ሦስት/APC3 ኢየሱስ ክርስቶስ 12 ይገባናል ማለት ነው፡፡ ልክ ወደ አብና ወደ መንፈስ ቅዱስ እንደምጸልይ ሁሉ ወደ እርሱምእንጸልያለን ማለት ነው፡፡ እናም እግዚአብሔር ራሱ ከኀጢአት እንደዋጀን በማወቅ ከድነት ዋስትናችን አንፃር ትልቅ መጽናናትንና እርግጠኝነትን እንይዛለን ማለት ነው፡፡ እነዚህና ሌሎችም በክርስትና ሕይወት ውስጥ የሚገኙ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች የሚያርፉት በክርስቶስ መለኮትነት ባለን እምነት ላይ ነው፡፡ ይህንን የኢየሱስን መለኮትነት በልቡናችን ይዘን፣ በሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ ውስጥ የእርሱ ሰውነት የተንፀባረቀበትን መንገድ ወደ መመልከቱ እንሻገራለን፡፡