የጌታ ኢየሱስ ትውልድ ግንድ ውስጥ ያለው የዘሩባቤል ልጅ የትኛው ነበር?
የጌታ ኢየሱስ ትውልድ ግንድ ውስጥ ያለው የዘሩባቤል ልጅ የትኛው ነበር?
በማቴዎስ ላይ ያለው አቢዩድ ወይንስ በሉቃስ 3.27 ላይ ያለው ሬስ እንዲሁም ደግሞ በ1ዜና 3.19-20 ላይ ያለውስ ዘሩባቤል?
ስለዚህም የሰላትያል ልጅ የዘሩባቤል ስም በማርያምም በዮሴፍም የዘር ሀረግ ላይ የመገኘቱ ነገር እኛን ሊያስደንቀን አይችልም፡፡ ማቴዎስ የነገረን ነገር የዮሴፍ አባት ስሙ ያዕቆብ ነበር በማለት ነው፡፡ በእርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ የያዕቆብ ልጅ ስለሆነ ሌላ ዮሴፍም ይነግረናል፣ እርሱም በግብፅ ውስጥ ሁለተኛውና በጣም ኃይለኛ ባለስልጣን ነበረ ዘፍጥረት 37-47፡፡ እነዚህ ሰዎች አንድና ተመሳሳይ ናቸው በማለት ልንናገር አያስፈልገንም ስለዚህም ሁለት የተለያዩ ሰዎች የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል ልጅ ተብለው ቢጠሩ ችግርን አይፈጥርብንም፡፡
ነገር ግን በ1ዜና 3.19-20 ላይ የተጠቀሰው ዘሩባቤል ሦስተኛው ሌላ ሰው ሊሆን ይችላል፡፡ እንደገናም ይህም ሁኔታ ችግርን አያመጣብንም ምክንያቱም ያ ስም የተለመደ ታዋቂ ስም ነበርና፡፡ በወንጌልም ውስጥ ማርያም የሚለው ስም የተለመደ ስም ስለነበር ማርያም ተብለው የተጠቀሱ ብዙ ሴቶች ነበሩ፡፡ ይህ በማቴዎስ 1.12፣13 ላይ የተጠቀሰው ዘሩባቤል የአጎት ልጅ ሆኖ ነው፡፡ የማቴዎስና የ1ኛ ዜና ንፅፅር የሚከተለውን የቤተሰብ የዘር ግንድ ሊሰጠን ይችላልና፡፡
ኢዮአኪን
|
ሰላትያልን --- ማልኪራም --- ፕዳያ --- ሸሃዛር --- ጃካሚያ --- ሆሻማ ---ንዳቢያ ---
| |
ዘሩባቤል ዘሩባቤል --- ሺማይ
| |
አቢዩድ ሰባት ወንዶች ልጆች
| (1 ዜና 3.19፣20)
|
ዮሴፍ